ከሕወሓት ጋር ምንም አይነት ድርድር አልጀመርኩም ሲል የኢትዮጵያ መንግስት ገለጸ ይሕ የተገለጸው በዛሬው እለት እየተካሄደ በሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3 ኛው አስቸኳይ ጉባኤ ነው። በጉባኤው መንግስት ከሕወሐት ጋር እያደረገ ነው የሚባለው ድርድር አሳታፊና ያልሆነና ግልጽነት የጐደለው ነው በሚል ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረበላቸው ጥያቄ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሕመድ በሰጡት ምላሽ ነው። ጥያቄው በተለይም ከተቃዋሚው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄን ወክለው የምክርቤት አባል በሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ የተነሳ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለዚሕ ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያዎ እስካሁን ከሕወሐት ጋር የተደረገ ድርድር አለመኖሩን ገልጸዋል። በእርስ በእርስ ጦርነት ፍጹም ድል የለም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ከዚህ አንጻር ውጊያውን ለማቆም ሌሎች አማራጮችን ማየት ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ አያይዘውም የሰላም አማራጭ ካለ ከሕወሐት ጋር ድርድር ማድረግ ክፋት እንደሌለው ገልጸው፤ ነገር ግን እስካሁን ከሕወሐት ጋር የተደረገ ድርድር የለም ብለዋል፡፡ ያማለት ግን ወደፊት ድርድር አይኖርም ማለት እንዳልሆነ አብራርተዋል፡፡እሳቸው ይህንን ይበሉ እንጅ የሕወሐቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከመንግስት ጋር በተዘዋሪ መንገድ ድርድር እያካሄደ መሆኑን በቅርቡ መግለጻቸው ይታወቃል። በአፍሪቃ ሕብረት ተወካይ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በኩልም ሁለቱ ...
ልጥፎች
ከፌብሩዋሪ, 2022 ልጥፎች በማሳየት ላይ