ከሕወሓት ጋር  ምንም አይነት ድርድር  አልጀመርኩም ሲል የኢትዮጵያ መንግስት  ገለጸ

ይሕ የተገለጸው በዛሬው እለት እየተካሄደ በሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛው አስቸኳይ  ጉባኤ ነው። በጉባኤው መንግስት ከሕወሐት ጋር እያደረገ ነው የሚባለው ድርድር አሳታፊና ያልሆነና ግልጽነት የጐደለው ነው በሚል ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረበላቸው ጥያቄ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሕመድ በሰጡት ምላሽ ነው።

ጥያቄው በተለይም ከተቃዋሚው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄን ወክለው የምክርቤት አባል በሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ የተነሳ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለዚሕ ጥያቄ በሰጡት  ማብራሪያዎ እስካሁን ከሕወሐት ጋር የተደረገ ድርድር አለመኖሩን ገልጸዋል።

 በእርስ በእርስ ጦርነት ፍጹም ድል የለም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ከዚህ አንጻር ውጊያውን ለማቆም ሌሎች አማራጮችን ማየት ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ አያይዘውም የሰላም አማራጭ ካለ ከሕወሐት ጋር ድርድር ማድረግ ክፋት እንደሌለው ገልጸው፤ ነገር ግን እስካሁን ከሕወሐት ጋር የተደረገ ድርድር የለም ብለዋል፡፡ ያማለት ግን  ወደፊት ድርድር አይኖርም ማለት እንዳልሆነ አብራርተዋል፡፡እሳቸው ይህንን ይበሉ እንጅ የሕወሐቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከመንግስት ጋር በተዘዋሪ መንገድ ድርድር እያካሄደ መሆኑን በቅርቡ መግለጻቸው ይታወቃል። በአፍሪቃ ሕብረት ተወካይ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በኩልም ሁለቱ  ተፋላሚ ሐይሎች  ችግሩን በሰላም እንዲፈቱ ለማደራደር  የሽምግልና ስራ ተጀምሮ እንደነበርም ይታወሳል።

ኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥ ሖናም ኢኮኖሚዋ አድጓል ተባለ

የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ጦርነቱን የተሸከመበት አቅም የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥ ሆናም ቢሆን በግብርና እና ከውጪ የሚገቡ ሸቀጦችን በውስጥ ምርት ለመተካት ያደረገችው ጥረት እና የተሰበሰበው ገቢ ከፍተኛ መሆንን በስኬት አንስተዋል።

ቂም እና ሌብነት የኢትዮጵያ የዘመናት የቁልቁለት ጉዞ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውን የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ዘላቂ ሰላም ለመገንባት ሲባል የሕወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩ ሰዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ መደረጉን ገልጸዋል።

እስካሁን ከሕወሐት ጋር የተደረገ ድርድር የለም። ይህ ማለት ግን ድርድር አይኖርም ማለት አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕወሐት ቀልብ ገዝቶ በጦርነት እንደማያሸንፍ ከተገነዘበ እኛ በደስታ ነው የምናየው በማለት ድርድር ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።

ብሔራዊ ውይይቱን በተመለከተም ትናንት የተሾሙት ኮሚሽነሮች ሁሉንም ማህበረሰብ ለማወያየት መደላደል ይፈጥራሉ። ውይይቶች መግባባት እንዲኖር ካላስቻሉ ግን ወሳኙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የየክልሎች ልዩ ሐይሎችን የመከላከያ ሰራዊቱ ተገዳዳሪ እየሆኑ መምጣታቸውንና የስጋት እና ምንጭ መሆናቸው ተጠቅሶ ለቀረበ ጥያቄም፤ ጥፋት ብቻ ሳይሆን ጥቅምም እንዳላቸው በመግለጽ ይሕ ሕገ መንግሥቱ የማያውቀው የየክልሎች የልዩ ሐይል አደረጃጀት ቀጣይ እንደሚሆን ባመላከተ ሁኔታ ምላሽ ሰጥተዋል። ዘገባውን ያደረሰን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰለሞን ሙጨ ነው።

ጠቅላይ ሚንስተር ዶክተር አብይ በሳእዲ የሚገኙ ስደተኞችን አስመልክቶ የሰጡት ምላሽ። 

ባለፉት ወራት ችግር ውስጥ ሆነንም ቢሆን በርካታ ኢትዮጵያዊያንን ከሳእዲ ወደሀገራቸው መልሰናል፤ ችግሩ የሳእዲ አረቢያ መንግስት እንደመንግስት ሪፎርም እየሰራ ነው፡፡

የሀገራቸው ዜጋ ስራ እንዲሰራ እና ኢኮኖሚያቸውን ለማሻሻል ከውጭ የመጡ ሰዎች የሚሰሩትን ስራዎች በራሳቸው ዜጎች ለማሰራት ፍላጐት አላቸው፤ ይህን ማድረጋቸው መብታቸው ነው፤ ተገቢነትም አለው፡፡

ከኢትዮጵያ በኩል ያለው ፈተና የእኛ ዜጎች በህገ ወጥ መንገድ የሔዱ መሆናቸው ነው፤ ሁሉም ፓስፖርት ያለው አይደለም፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፤ ሁሉም ከዚህ ወደሳእዲ የሄደ ስለመሆኑም ለማወቅ ያስቸግራል፡፡ ቁጥሩም ከፍተኛ ነው ወደ 1 መቶ ሺህ የሚጠጋ ነው፡፡ ስለዚህ መከራም አብሮ እንዳይመጣ ቆም ብሎ ማጥናት ይፈልጋል፡፡

ከሳእዲ መንግስት ጋር በቅርበት እየሰራን ነው፡፡ በቅርቡም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ቡድንም ተቋቁሟል፤  በደንብ አጥንተን ዜጎቻችንን ወደሀገራው እንመልሳለን፤ ስንመልስ ጥፋት የሚያስከትሉ ሰዎች ካሉበት ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡

መንግሥት ባለፉት ስድስት ወራት 297 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን አስታወቀ!

በጦርነትና ሌሎች ውስብስብ ችግሮች ውስጥ በከረመችው ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሚባል ገቢ ቢሰበሰብም መንግሥት ባለፉት ስድስት ወራት 297 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

የባለፉት 6 ወራት አገራዊ ወጪ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 39 በመቶ እድገት እንዳለውም አመላክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሳወቁት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ ነው።

ያለፉት ስድስት ወራት የጦርነት ወቅት በመሆናቸው ምጣኔ ሃብቱ ላይ በዘርፈ ብዙ ፈተናዎች የታጠረ እንደነበርም አውስተዋል፡፡

በጠርነት ወቅት ብድር የሚሰጡ አገራት እና ተቋማት ብድር መስጠቱን፤ እርዳታ የሚያደርጉ ደግሞ እርዳታን ያዝ የማድረግ ሁኔታቸው ከፍ ስለሚሆን ምጣኔ ሓብቱን በእጅጉ ይጎዱታል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም አምራቹ ሓይል በሙሉ ሓይሉ ከማምረት ይልቅ አንድም በአካል አሊያም በሐሳብ ወደ ጦርነቱ መግባቱ፣ የዜጎች መፈናቀል፣ መገደል፣ መደፈር፣ መዘረፍ በስፋት መኖሩ ያለፉት ስድስት ወራት የምጣኔ ሃብቱ ተግዳሮቶች እንደነበሩም አስረድተዋል፡፡

ይህም ሆኖ ባለፉት 6 ወራት 185 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 171 ነጥብ 3 ቢሊዩኑን መሰብሰብ ወይም የእቅዱን 92 በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ይህ ገቢ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ሲታይ 15 በመቶ እድገት እንዳለውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡ ይሑንና የመንግሥት ወጪ 297 ቢሊዮን ብር በላይ እንደነበረም ነው ያሳወቁት።

 ከኢትዮጲያ ነዳጅ በቦቴ ይዞ ሲወጣ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ ነዳጁን ጨምሮ ቦቴው እንደሚወረስበት ተገለጸ !!

 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው እየሰጡ በሚገኘው ማብራሪያ ኢትዮጲያ ከፍተኛ ወጪ የምታወጣበት ነዳጅ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጪ ወጥቶ የሚሸጥበት መንገድ በመኖሩ ከፍተኛ ጫና ተፈጥሯል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

ይሕንን መሰል ሕገ ወጥ ተግባር በመከላከል ረገድ ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሰል ተግባራት በክልላቸው ሲፈጸም ካገኙ በአፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ አሳስበዋል ፡፡

በእርምጃውም የክልል ፖሊስን ጨምሮ ልዩ ሐይሎች መሰል ሕገ ወጥ ተግባር ሲፈጸም ያገኙትን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ከማዋል ባለፈ ነዳጁን ጨምሮ ነዳጅ የጫነውን ቦቴው ሳይቀር መውረስ እንደሚችሉ ጠቁመዋል ፡፡

 ሸኔን ህዝቡ ለምን  ተሸከመው?  ብሎ መጠየቅ ይገባል ›› አሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ 

ከኦሮሞ ህዝብ እና  ከጸጥታ ሐይሎች ጋር በደንብ መነጋገር ይፈልጋል ብለዋል፡፡

‹‹ ወታደራዊ  እና ፖለቲካዊ ስራውን አስታርቆ  መሄድ እንደሚያስፈልግ፣ እንዲሁም ችግር ካለም ማየት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ሸኔን ለማጥፋት ወታደራዊ ስራ ብቻውን የሚያመጣው ለውጥ የለም›› ሲሉም አክለዋል፡፡

ሕዝቡ ለምን ተሸከመው ? ለምንድነው የሆነ አንድ ወረዳ የቀለበው የደበቀው? ምን ችግር ስላለ ነው?  የሚለውን ቀርቦ  መነጋገር እንደሚያስፈልግ አንስተዋል ፡፡

‹‹ አሁን ለምን በረታ ለምን ጉልበት አወጣ የሚሉ አሉ፡፡ ምክንያቱም ብዙ ደጋፊ ስላለ ነው፤ አሁን ብዙ አሰልጣኝ አለው ብዙ አስታጣቂ ፤ብዙም ገንዘብ ሰጪ››  አለው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ ሸኔ አላማ የለውም ፡፡ ምንም የተጻፈ ነገር የሌለው መሪ አልባ ነው›› ብለውታል፡፡

‹‹ለኦሮሞ ህዝብ እታገላለሁ የሚል አንድ ቡድን እንዴት የኦሮሞን ህዝብ ልማት ያወድማል?››  ሲሉም ይጠይቃሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

‹‹ቡድኑ አንድ ቦታ ሆኖ የሚዋጋ አይደለም ህዝብ እና ወታደር ከተባበረ ግን ችግሩ ይፈታል››  ብለዋል፡፡

ሸኔም፤ ሕውሓትም ቤኒሻንጉልም ሌላውም ኃይል ግን ፍጹም ኢትዮጵያን አያሽፍም ይህ ከንቱ ፍላጎት ከንቱ ድካም ነው፡፡

ሰው ሊገድል ይችላል ግን አያሸንፍም፡፡ መግደሉን እንዲያቆም በተባበረ ክንድ  መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸው መካስስ ሳይሆን ተባበሩ እንዲህ አይነቱን ነገር ማስቆም ይቻላል ነው ያሉት።

‘‘ጦርነት የአለም ኃያላን ሀገራት እንደማያዋጣችው በመረዳት፤በአንድ እጃቸው ጥንቃቄን በአንድ እጃቸው የድርድር ሐሳብን በመያዝ በአገር እና በሕዝብ መካከል ሰላምን ለማምጣት እየጣሩ ነው ''  ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ 

ጠቅላይ ሚኒስትር / አብይ አሕመድ በዛሬው እለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰተዋል፡፡

‘‘ አይደለም ኢትዮጵያ ታላላቅ የአለም ሓያል አገራት ጦርነት እንደማያዋጣችው በመረዳት፤በአንድ እጃቸው ጥንቃቄን በአንድ እጃቸው የድርድር ሐሳብን በመያዝ በአገር እና በሕዝብ መካከል ሰላምን ለማምጣት ይጓዛሉ ኢትዮጵያም ይሕን ልታደርግ ይገባታል'' ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ 

ከሕውሐት ጋር ድርድር ይደረጋል በሚባለው ጉዳይ ላይ እርሶ ምን ይላሉ ብለው የምክር ቤት አባል ለተጠቁት ጥየቄ ፤ጠቅላይ ሚንስተሩ ‘‘አለማችን 3 500 አመታት ውስጥ ያለ ግጭት በሰላም ያሳለፈቸው 265 አመታትን ብቻ ነው ያሉት፡፡

በተሰራው ጥናት መሰረት በአለማችን ላይ 3 500 መቶ አመታት ውሰጥ 1450 ጦርነቶች መደረጋቸውን አንስተዋል፡፡

‘‘ከተደረጉ 1450 ጦርነቶች መካከል 215 ጦርነቶች ወታደራዊ ግጭቶች ናቸው ያሉ ሲሆን፤ በነዚህ አመታት ውስጥ በተደረጉ ግጭቶች ምክኒያት 3.4 ቢሊዮን ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል'' ነው ያሉት ፡፡

‘‘በኢትዮጵያም በርካታ የግጭት ታሪኮች አሉ፤ በተለይ ባለፉት 34 አመታት  የተደረጉ ጦርነቶች አገሪቱን በኢኮኖሚ ደክማ እንድትቀር የሚያደርጋት ከመሆኑም በዘለለ፤ በሕዝቦች መካከል መለያየትን የፈጠረ ነበር ለዚህም ማሳያ ኤርትራን መጥቀስ ይቻላል '' ብለዋል፡፡

 ትሩዝ ሶሻል የተባለው አዲስ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ መተግበሪያ ለአገልግሎት ቀረበ።

 በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኩባንያ የተሰራው እና «ትሩዝ ሶሻል» የተባለው አዲስ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ መተግበሪያ «አፕል ስቶር» ላይ በማውረድ መጠቀም እንደሚቻል በመተግበሪያው ድረ ገጽ የወጣው መረጃ ያሳያል።።

መተግበሪያው ለፖለቲካ ርእዮተ ዓለም ሳይወግን ክፍት፣ ነጻ እና ታማኝ ዓለም አቀፍ የውይይት መድረክን የሚያበረታታ ትልቅ የአሜሪካ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ነው ተብሏል።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት በተደጋጋሚ የተበረታታውን ሕዝባዊ የካፒቶል ሂል ተቃውሞ እና ጥቃት ተከትሎ «ተጨማሪ ሐይልን በማነሳሳት ስጋት» ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ እና ትዊተርን የመሳሰሉ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ከዓለፈው አመት ጀምሮ ዶናልድ ትራምፕን ከተሳትፎ ማገዳቸው ይታወቃል።

አዲሱ ወደ ማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ዶናልድ ትራምፕን ወደ መድረኩ ይመልሳቸዋል ተብሏል።

 ቤተሰቦች ከተመቻችሁ ላይክ : ለሌሎች እንዲደር ሸር ያድርጉ : ሰብስክራይብ ካላደረጋችሁ ሰብስክራይብ በማድርግ እና የደውል ምልክቶን በመጫን : የቻናላችን ቤተሰቦች ይሁኑ : ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ : ኮመንት ላይ ስቀምጥሉን : ቤተሰቦች እኛን መርጣችሁ : አብራችሁን ስለቆያችሁ : እናመሰግናለን።

አስተያየቶች